Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከዛሬ ጀምሮ የነዳጅ ክፍያ በሩብል እንዲሆን ደነገገች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ሀገራቸው ነዳጅ በሩብል ለመሸጥ የሚያስችላትን ድንጋጌ ፈረሙ፡፡

ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ÷ ሀገራት ከዛሬ ጀምሮ በሩሲያ ባንኮች አካውንት እንዲከፍቱና የነዳጅ ሽያጭ ክፍያቸውን በሩሲያ መገበያያ ገንዘብ ሩብል እንዲፈጸም አሳስበዋል፡፡

ይህን የማይቀበሉ የሩሲያ አጋር ያልሆኑ ሀገራት በሩብል መክፈል ወይም ችግራቸውን በራሳቸው መንገድ መፍታት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ሩሲያ ስታቀርብ የነበረው ነዳጅ የአውሮፓን የነዳጅ ፍጆታ 40 በመቶ ያህል እንደሚሸፍን ነው የተመለከተው፡፡

ምንም እንኳን የምዕራቡ ሀገራት በሩሲያ ላይ የምንዛሬ ልውውጥ ማዕቀብ ቢጥሉም፣ ሩሲያ ክፍያዎችን በመገበያያ ገንዘቧ ሩብል የምትጠይቅ ከሆነ የተዳከመው ኢኮኖሚዋ በተዘዋዋሪ እንደሚያንሰራራ ነው የተመለከተው፡፡

ቭላድሜር ፑቲን ሐሙስ በፈረሙት ድንጋጌ ÷ ሀገራት ነዳጅ ከሩሲያ መግዛት ሲፈልጉ ክፍያዎችን የሩሲያ መንግስት ኢነርጂ ኩባንያ አካል በሆነው “ጋዝፕሮም ባንክ” በኩል በውጪ ምንዛሬ እንዲያስተላልፉ እና ባንኩ ወደ ሩብል ቀይሮ ግዢ እንዲፈጽም ያዛል።

የጀርመን ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ሮበርት ሀቤክ ÷ የፑቲንን እርምጃ ኮንነዋል።

ሀገራቸው ማናቸውንም አይነት ችግሮች ለመወጣት አስቀድማ በመዘጋጀቷ ሩሲያ ወደ አውሮፓ የሚሄደውን ነዳጅ ብትዘጋ እንኳ እንወጣዋለን ብለዋል፡፡

ጣሊያን በበኩሏ ከአውሮፓ አጋሮቿ ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላትና ችግሩን እንደምትወጣ በመጥቀስ አስፈላጊ ከሆነም ለችግር ጊዜ አከማችታ ያስቀመጠችውን ነዳጅ እንደምትጠቀም ነው የገለጸችው፡፡

በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ÷ እየናረ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ለማረጋጋት በየቀኑ 1 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ለሚቀጥሉት 6 ወራት እንደሚያቀርቡ ማስታወቃቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.