Fana: At a Speed of Life!

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ አየር ኃይል ለከፍተኛ መኮንኖች የማዕረግ እድገት ሰጥቷል።

አየር ኃይሉ በዛሬው እለት በቢሾፍቱ በሚገኘው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ባካሄደው ስነ ስርዓት ላይ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ እና የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በስነ ስርዓቱ ላይ 106 ለሚሆኑ መኮንኖች በአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የተለያዩ የማዕረግ እድገቶችን ሰጥተዋል።

ከዚህ ባለፈም ላለፉት 6 ወራት በስልጠና ላይ የቆዩ የአየር ኃይል ወታደራዊ ፖሊስ አባላትም በዛሬው እለት ተመርቀዋል።

በተጨማሪም ባለፉት ስድስት ወራት በተቋሙ ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ሰራተኞችም የእውቅና እና ሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርአት ተካሄዷል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.