Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በተደረገላቸው ሕክምና ዕይታቸው ተመለሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኦርቢስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በሰጠው ሕክምና ከ1 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ዕይታቸው መመለሱን አስታወቀ።

በዘመቻው የመድኃኒት ሕክምና፣ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ሕክምና፣ የዐይን ቆብ መቀልበስ ቀዶ ጥገና ሕክምና እና የመነጽር ልኬታ እና እደላ መደረጉን የኦርቢስ ኢንተርናሽናል ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰማልኝ አበው ገልጸዋል።

በስድስት ወራት ውስጥ ከ52 ሺህ በላይ ሰዎች አጠቃላይ የዐይን ሕክምና አገልግሎት ማግኘታቸውም ተመላክቷል።

ሕክምናው በሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር ዞኖች በሚገኙ 11 ወረዳዎች የተሰጠ ሲሆን፥ ከታካሚዎች ውስጥ 1 ሺህ 228 ሰዎች የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸው ሙሉ በሙሉ ዕይታቸው ተመልሷል ተብሏል።

በአማራ ክልል 360 ሺህ ዐይነ ስውራን እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት በሕክምና መዳን የሚችሉ በመሆናቸው ሕክምናውን በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዘግቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.