Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል መንግስት ለ2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ተኪኡ ምትኩ በሰጡት መግለጫ፥ የክልሉ መንግስት የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ 2 ሺህ 332 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን ተናግረዋል።

አያይዘውም ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ጥሩ ስነ ምግባር ያሳዩና በጥፋታቸው የተፀፀቱ መሆናቸውን አንስተዋል።

በዚህም የይቅርታ ህጉን አሟልተው ለተገኙ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓልም ነው ያሉት።

ታራሚዎቹም በጥፋታቸው ተፀፅተው የሚቀላቀሉትን ማህበረሰብ እንደሚክሱ እምነታቸው መሆኑንም ገልጸዋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው ታራሚዎች ውስጥም 46ቱ ሴቶች መሆናቸውም ታውቋል።

በዮናታን ግዛቸው

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.