በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ሊሻገሩ የነበሩ 96 ሴቶች ተያዙ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ለመሻገር የሞከሩ 96 ሴቶች መያዛቸውን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።
ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች የመጡት ሴቶች ጎንደር ከተማ ባረፉበት ሆቴል ውስጥ ከህብረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ መያዛቸውን፥ የጎንደር ከተማ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ የስልጠናና ግንዛቤ ማስጨበጥ ንዑስ ክፍል ሀላፊ ዋና ሳጅን ታደሰ አለምነህ ተናግረዋል።
አሁን ላይም ሁሉም ሴቶች በፖሊስ ጣቢያው የሚገኙ ሲሆን፥ የአካባቢው ነዋሪዎችም የምግብ እና ሌሎች ድጋፎችን እያደረጉላቸው ይገኛልም ነው ያሉት።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም አንድ ወንድ እና ከስደተኞቹ ጋር የነበረች ሴት በተጠርጣሪነት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋልም ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል።
አያይዘውም ህገ ወጥ ደላሎች በአዲስ አበባ በኩል የሚደረጉ ጉዞዎች ተከልክለዋል በሚል የስደት ተጓዞቹን ወደ ጎንደር በምሽት በመላክ ከ15 እስከ 20 ሺህ ብር እንዳስከፈሏቸውም ጠቅሰዋል።
በምንይችል አዘዘው
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision