Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ም/ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንስ ቲመርማንስ ጋር ተወያዩ።

በቆይታቸውም የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ህብረት የትብብር መስኮች ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል።

በዚህም በዋናነት በታዳሽ ሀይል፣ በአየር ንብረት እና በውሃ አቅርቦት ስርዓት፣ በደን ልማት፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም ሌሎች ዘርፎች ላይ መወያየታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

በውይይቱም የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንስ ቲመርማንስ የኢትዮጵያ መንግስት በዘርፉ ያከናወናቸውን ተግባራት አድንቀዋል።

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በቀጣይ ጊዜያትም በዘርፉ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.