Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የደንበኞቻቸውን የቦታ መረጃ አሳልፈው የሰጡ የአሜሪካ ሞባይል ስልክ አገልግሎት አቅራቢዎች ይቀጣሉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፌደራል ኮሙዩኒኬሽን ኮሚሽን የደንበኞቻቸውን የቦታ መረጃ አሳልፈው የሰጡ የሞባይል ስልክ አገልግሎት አቅራቢዎችን 200 ሚሊየን ዶላር ሊያስከፍል እንደሚችል ተጠቆመ።

ይህ ቅጣት ይጠብቃቸዋል የተባሉት ኩባንያዎች ቨሪዞን ኮሙዩኒኬሽን ፣ አይቲ ቲ፣ ስፕሪንት እና ቲ ሞባይል ናቸው።

በፈረንጆቹ 2018 የወጣ የምርመራ መረጃ የቦታ መረጃዎች ለስልክ ተጠቃሚዎች የመንገድ አቅጣጫ እና የጤና አገልግሎት ከማሳወቅ ባሻገር ተገቢ ላልሆነ አገልግሎት ሲውሉ እንደነበረ ያመላክታል።

በዚህም በስልክ ላይ የሚገኝ የቦታ መረጃ በሶስተኛ ወገን መገኘቱ ነው የተነገረው።

በጉዳዩ ዙሪያ የስልክ አገልግሎት አቅራቢዎቹ ምንም አይነት ምላሽ ያልሰጡ ሲሆን ቲ ሞባይል ግን ከፍተኛ ቅጣት እንደሚጣልበት ተነግሯል።

ይህ ቅጣት በኮሚሽኑ ባለፉት አስርት ዓመታት ከተላለፉት ትልቁ እንደሚሆን እና ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሚተላለፍ የመጀመሪያው ቅጣት እንደሆነም ተጠቁሟል።

ከቦታ መረጃ ጋር ተያይዞ ያለው ንግድ በ100 ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚነካ በመሆኑ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱም ነው የተነገረው።

ምንጭ፡-siliconangle.com እና new york times

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.