Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 50 ተሽከርካሪዎች መቀሌ እንዲደረሱ ያደረገውን ጥረት አደነቀች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 8 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ 50 ተሽከርካሪዎች መቀሌ እንዲደረሱ ያደረገውን ጥረት አድንቋል፡፡
 
የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ጉዳዩን አስመልክተው ባወጡት መግለጫ÷በትግራይ ክልል ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች 1 ሺህ 700 ሜትሪክ ቶን የሰብዓዊ እርዳታ መቀሌ እንዲደርስ ጥረት ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል፡፡
 
ከዚህም ባለፈ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጥላ ስር የሚገኙ እና ሌሎች የሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ለማዳረስ የሚያደርጉትን ያላሰለሰ ጥረት አድንቀዋል፡፡
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ያደረገውን የግጭት ማቆም ውሳኔም የሚበረታታ መሆኑም ጠቁመዋል፡፡
 
በቀጣይም በጦርነቱ ምክንያት በሁሉም አካባቢዎች ችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች አስፈላጊው የሰብዓዊ እርዳታ እንዲሰራጭ ምቹ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.