Fana: At a Speed of Life!

35 ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 35 ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ መስጠሟን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አስታወቀ።
ጀልባዋ በሜዲትራንያን ባህር ምዕራባዊ የሊቢያ የባህር ዳርቻ አካባቢ መስጠሟንም ገልጿል።
እስካሁን የስድስት ሰዎች አስከሬን የተገኘ ሲሆን ቀሪዎቹን የማፈላለግ ስራው እንደቀጠለ መሆኑንም አስታውቋል።
በዚህ ሳምንት ብቻ 53 ስደተኞች በሊቢያ ባህር ዳርቻዎች ለህልፈት ተዳርገዋል አልያም ጠፍተዋልም ነው ያለው ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ።
መነሻቸውን ሊቢያ ያደረጉ ስደተኞች በተደጋጋሚ በሚያደርጉት የባህር ላይ ጉዞ ለህልፈት እንደሚዳረጉ ቲ አር ቲ በዘገባው አስታውሷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.