Fana: At a Speed of Life!

በአየርላንድ፣ ኢኳዶር፣ አርሜኒያና ኳታር አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቨይረስ ስርጭት እየጨመረ የመጣ ሲሆን፥ በአየርላንድ፣ኢኳዶር ፣አርሜኒያ እና ኳታር አዲስ ቫይረሱ ተጠቂዎች መገኘታቸው ተገልጿል።

መነሻውን ከቻይና ውሃን ግዛት አድርጎ የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ በርካታ ሃገሮችን እያዳረሰ ይገኛል።

በዚህም ትናንት እና ዛሬ በአየርላንድ፣ ኢኳዶር ፣አርሜኒያ እና ኳታር አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኝተዋል።

ተጠቂዎቹም በሽታው ከተቀሰቀሰባቸው ጣሊያን ፣ ስፔን እና ኢራን የተመለሱ መሆናቸው ነው የተገለፀው።

የቫይረሱ ተጠቂዎች  ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን፥ ከእነሱ ጋር ንክኪ የነበራቸውም ሰዎችም ወደ መቆያ ስፍራ መግባታቸው ታውቋል።

አሜሪካ፣ ታይናንድ እና አውስትራሊያም በሀገራቸው በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያውን ሞት አስመዝግበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀሰቀሰባት ቻይና በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 79 ሺህ 968 የደረሰ ሲሆን፥ 2 ሺህ 873 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል።

እንዲሁም 41 ሺህ 675 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ከቻይና ውጪ በአጠቃላይ በኮሮና ቨይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ የደረሰ ሲሆን፥ 105 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

በዚህም በሽታው በስፋት ከተሰራጨባቸው ሀገራት  ደቡብ ኮሪያ ፣ኢራን እና ጣሊያን  ይገኙበታል።

ምንጭ፡-ሲ.ጂ.ቲ.ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.