Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ለፖላንድ እና ቡልጋሪያ የምታቀርበውን ጋዝ አቋረጠች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ለፖላንድ እና ቡልጋሪያ ስታቀርብ የነበረውን ጋዝ ማቋረጧን አስታውቃለች፡፡
 
የሩሲያው ግዙፍ የነዳጅ ተቋም ጋዝፕሮም እንዳስታወቀው÷ ከሩሲያ ወደ ፖላንድ እና ቡልጋሪያ ሲላክ የነበረው የጋዝ አቅርቦት ከዛሬ ጀምሮ ተቋርጧል፡፡
 
አቅርቦቱ የተቋረጠው አገራቱ ክፍያውን በሩሲያ የአገር ውስጥ መገበያያ ገንዘብ (ሩብል) ለመፈጸም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው ተብሏል፡፡
 
ተቋሙ ፖላንድ አና ቡልጋሪያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቱን የሩሲያ ነዳጅ ዘይት ሽያጭ በሩብል እንዲፈጸም የወሰኑትን ውሳኔ እስካላከበሩ ድረስ አቅርቦቱ ተቋርጦ እንደሚቆይ አስታውቋል፡፡
 
የሁለቱ አገራት የኢኮኖሚ ሚኒስትሮችም ሩሲያ የጋዝ አቅርቦቱን እንዳቋረጠች የሚያሳውቅ ደብዳቤ የደረሳቸው መሆኑን እንዳረጋገጡ አር ቲ ዘግቧል፡፡
 
ሩሲያ ከዩክሬን ግጭት ጋር ተያይዞ በአሜሪካ እና ምዕራባውያን የተጣለባትን ማዕቀብ ለመቋቋም የነዳጅ ዘይት ሽያጭ በሩብል እንዲሆን መወሰኗ የሚታወስ ነው፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.