Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ መድሃኒቶች ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ስምምነትን ፈረመች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የአፍሪካ መድሃኒቶች ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ስምምነትን ፈረመች፡፡
 
ስምምነቱን በአፍሪካ ህብረት በመገኘት የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፈርመዋል።
 
በስነ ስርዓቱ ላይ ዶክተ ሊያ ኢትዮጵያ የኤጀንሲው አባል መሆኗ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።
 
የአፍሪካ ህብረት ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ በበኩላቸው ÷ ስምምነቱ የተመጣጠነ የመድኃኒት አቅርቦት እና የቁሳቁስ ስርጭት በአፍሪካ አስተማማኝ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።
 
በፊርማ ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ መገኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በ32ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ የአፍሪካ መድሃኒቶች ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ስምምነትን ተቀብሎ ማጽደቁ ታወሳል፡፡
 
ስምምነቱ በፈረንጆቹ ጥቅምት 5 ቀን 2021 ዓ.ም.ወደ ስራ ለመግባት የሚያስችለውን የ15 አባል ሃገራት ፊርማ ማጽደቅን ተከትሎ ህዳር 5 ቀን 2021 ዓ.ም.ወደ ስራ ገብቷል።
 
ስምምነቱ ተፈፃሚ እንዲሆን ኢትዮጵያ በምታከናውናቸው የጤና ዘርፍ መሻሻል እና የህዝብ የጤና ተቋማት ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ መሰል አይነቱ አህጉር አቀፍ ተቋማት መመስረታቸው ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.