Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በሐዋሳ ከተማ ተገንብተው የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን መረቁ፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ ÷ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ ፣የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የሐዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሱ አሩሳ ተገኝተዋል።

ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ከሆኑ ፕሮጀክቶች መካከል ከ80 ሚሊየን በላይ ወጪ የተደረገበት ከቱላ ዳካ የ17 ኪሎ ሜትር ዘመናዊ የመንገድ ዳር ማብራት፣የአላሙራ ሁለተኛና መሠናዶ ትምህርት ማስፋፊያ ህንፃዎች እንዲሁም ዘመናዊ የከተማ አስፋልት መንገድ ግንባታዎች እንደሚገኙ ከክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.