ከዒድ እስከ ዒድ ወደ አገር ቤት ጥሪ የመከፈቻ መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከዒድ እስከ ዒድ ወደ አገር ቤት ጥሪ የመከፈቻ መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ እየተካሄደ ነው፡፡
በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም ጥሪውን ተቀብለው የመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በመርሐ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል::
ዛሬ በተጀመረው መርሐ ግብር እስከ ኢድ ኢድ አልፈጥር ድረስ የተለያዩ ጥቅል መርሐ ግብሮች ለዳያስፖራዎች እንደተዘጋጁ ተገልጿል::
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በሄድንበት ስለ ሰላም መስበክ ይኖርብናል፤ በመተባበርም ለአገር እድገት ልማት ማሰብ ያስፈልጋል ብለዋል::
በዘቢብ ተክላይ