Fana: At a Speed of Life!

አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂውማን ራይትስ ዎች “ሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል” በሚል ያወጡት ሪፖርት ተጨባጭነት የሌለውና አሸባሪውን ህወሓት የሚደግፍ ነው – በአሜሪካ የኢትዮጵያ ሲቪክ ተቋማትና አደረጃጀቶች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂውማን ራይትስ ዎች በወልቃይት አካበቢ “የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል” በሚል ያወጡት ሪፖርት ተጨባጭነት የሌለው እና ለአሸባሪው ህወሓት ያደላ መሆኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ሲቪክ ተቋማት፣ የዳያስፖራ አደረጃጀቶችና በልዩ ልዩ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ገለፁ።

ሁለቱ ተቋማት ባወጡት የጋራ ሪፖርት ÷ “ምዕራብ ትግራይ” ብለው በጠቀሱት ስፍራ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል በሚል መንግስትን፣ የአማራ ክልል መስተዳድርን፣ የአማራ ክልል ሚሊሻን እና ፋኖን በሪፖርታቸው መወንጀላቸው ይታወሳል።

መቀመጫቸውን በአሜሪካ እና በተለያዩ ሀገራት ያደረጉ 37 ተቋማት እንዲሁም 193 ኢትዮጵያውያን ምሁራን ለሪፖርቱ በጋራ ባወጡት መግለጫ ምላሽ ሰጥተዋል።

በምላሻቸውም ÷ “አምነስቲ ኢንተርናሽናል “ እና “ሂውማን ራይትስ ዎች” ጭካኔ የተሞላበት የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈጽሟል በሚል ያወጡት ሪፖርት ተጨባጭ እውነታ የሌለው፣ ለአሸባሪው ህወሓት ያደላ ፣ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማካተት የቀረበ መሆኑን አመላክተዋል።

በሁለቱ ተቋማት የቀረበው ሪፖርት ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው ሰዎች ጀምሮ ጥናቱ እስከ ተካሄደበትና ይፋ እስከሆነበት ወቅት ድረስ ሳይንሳዊና ሙያዊ ሃላፊነት የጎደለው ነውም ብለዋል ።

ሪፖርቱ በአሸባሪነት የተወገዘውን የህወሓትን ቡድን ወደ ሥልጣን ለመመለስና በወልቃይት ህዝብ ላይ አሸባሪው የፈጸመውን የጅምላ ግድያ ለመሸፈን ተቋማቱ ጊዜ ጠብቀው ያወጡት የአቋም መግለጫ መሆኑንም ጠቅሰው የሁለቱን ተቋማት ሪፖርት ተቃውመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.