Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በሰሜን ሶሪያ የነበሩ ወታደሮቿን ወደ ኢራቅ ማዛወሯ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ በሰሜን ሶሪያ ተሰማርተው የነበሩ ወታደሮቿን ወደ ኢራቅ ማዛወሯ ተገለ።

የአሜሪካ ወታደራዊ ተሸካርካሪዎች የጢገርስ ወንዝን አቋርጠው በቱርክ አዋሳኝ ፊሽካሃቡር የኩርዶች ይዞታ መዲና ወደ ሆነችው የኢርቢል ከተማ ወደ ሚገኘው የጦር ሰፈር ማምራታቸው ተነግሯል።

ከዚህም ሌላ በሳሃላ ወሰን ሰሜን ኢራቅ ዶሁክ ግዛት በኩል የአሜሪካ ወታደሮች ከሰሜን ሶሪያ ወደ ኢራቅ መግባታቸውን አይን እማኞች ገልጸዋል።

በዚህም 100 የአሜሪካ ወታደራዊ ተሸካርካሪዎች መግባታቸውን የሬውተርስ ካሜራ ባለሙያን ጠቅሰው የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የአሜሪካ ወታሮች ከሰሜን ሶሪያ መውጣት በብዛት ኩርዶች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ተቃውሞን አስተናግዷል ነው የተባለው።

ነዋሪቹ የአሜሪካን ቃል አባይነት ድምፃቸውን ከፍ አድረገው በመግለጽ ወታደራዊ ተሸከርካሪቹ ላይ ሲወረውሩ ታይተዋል ነው የተባለው።

ረጅም እድሜ ለኩርድ ዋይ ጂ ፒ ታጣቂዎች የሚሉ መፈክሮችንም አንግበው የአሜሪካ ተሸከርካሪዎች በሚያልፉበት ጎዳናዎች ላይ መታየታቸውም ተገልጿል።

የአሜሪካው የመከላከያ ሚኒስትር ማይክ ኢስፔር በሰሜን ሶሪያ በኩርድ ታጣቂዎች የሚመራው የሶሪያ ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች የነዳጅ ዘይት ይዞታ አከባቢ የተወሰኑ የአሜሪካ ወታደሮች እንደሚቆዩ ተናግረዋል።

የወታደሮቹ በዚያው መቆየትም የአይ ኤስ የሽብር ቡድን የነዳጅ አከባቢውን መልሶ በመቆጣጠር የገቢ ምንጭ እንዳያገኝ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

ባሳለፍነው ሳምንትም ከማንቢጅ ከተማ እና ከኮባኔ የቱርክ ወሰን ጨምሮ ከሶስት የጦር ሰፈሮች የአሜሪካ ወታደሮች መውጣታቸውን ዘገባው አስታውሷል።

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.