Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር የሚያስችል በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል 1 ሺህ 443ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም እንዲከበር የሚያስችል በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት÷ በየደረጃው ያለው የጸጥታ ኃይል በዓሉ በሰላም እንዲከበር በቂ ዝግጅት አድርጓል።
የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮችምተቀናጅተው አካባቢያቸውን እየጠበቁ መሆኑን ጠቁመው÷ የሁለቱ እምነት ተከታዮች የኢድ አልፈጥር በዓል የሚከበርባቸውን ቦታዎችና መስጂዶችን እያጸዱ መሆኑንና ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን አካባቢያቸውን በንቃት እየጠበቁ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
በጎንደር ከተማ ሙስሊምና ክርስቲያኑ አንድ ሆነው በዓል የሚያከብሩበት እሴታቸውን ለመሸርሸር ያለመ በጥቂት ቡድኖች የተቀነባበረ ግጭት እንዲፈጠር መደረጉን አመልክተዋል።
“በጎንደር ከተማ የተከሰተው ግጭት የማንኛውንም እምነት የማይወክል ስለሆነ በሕዝቦች አብሮነት ላይ ጥያቄ ሊያስነሳ አይችልም” ነው ያሉት አቶ ደሳለኝ።
የገጠመንን ፈተና ማለፍ የሚቻለው በጋራ በመቆም ነው ያሉት ኃላፊው÷ ሕዝቡም ከጸጥታ ኃይሉ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.