Fana: At a Speed of Life!

ባለስልጣኑ ከቅርሶች እድሳት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የተጠናከረ ስራ መጀመሩን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣2012 (ኤ ቢ ሲ) በሀገሪቱ ከሚገኙ ቅርሶች እድሳት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የተጠናከረ ስራ መጀመሩን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን አሰታውቋል።

የባለስልጣኑ የቅርስ ጥበቃና እንክብካቤ ዳይሬክተር አቶ ሃይሉ ዘለቀ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ በተለያዩ ምክንያቶች ጉዳት የደረሰባቸውን ቅርሶች የቀደመ ይዘታቸው ሳይቀየር ለማደስ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
 
በዚህ መሰረትም የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትና የጢያ ትክል ድንጋይ እድሳት በተጠናከረ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን ነው ዳይሬክተሩ የገለጹት።
 
በሌላ በኩል የፋሲል አብያተ መንግስታትን እድሳት ስራ ማከናወን የሚያስችል የቅድመ ጥገና ጥናት ለመጀመር ዝግጅት እተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን በዘላቂነት ለማደስም ከፈረንሳይ መንግስት ጋር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ለእደሳቱ ስራ የሚደረገው ጥናት መጀመሩን የገለጹት አቶ ሃይሉ ፥ ይህም እስከ ታህሳስ 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ አንስተዋል።

የጥናት ውጤቱን ተከትሎም ተግባራዊ የጥገና ስራው ይጀመራል ብለዋል።

በሹመት አለማየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.