Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዩኒሊቨር ኢትዮጵያ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከዩኒሊቨር ኢትዮጵያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ዩኒሊቨር ኩባንያ በዓለም በበርካታ አገራት የንጽህና የውበት መጠበቂያ ዕቃዎችን እና ምግብ ነክ ምርቶች በማምረት የሚታወቅ ሲሆን÷ ከሰባት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ በኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ስራ መጀመሩን የስራ ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡
ድርጅቱ በአሁኑ ጊዜ ከ7 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩን እና በቀጣይም የተጀመሩ ስራዎችን ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳላቸውም በውይይታቸው ወቅት ተመላክቷል፡፡
ከአገር ውስጥ የሚገኙ ጥሬ ዕቃዎች በስፋት በመጠቀም ምርቶቻቸውን ከአገር ውስጥ ገበያ በተጨማሪ ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ በአፍሪካ ኢትዮጵያ ቀዳሚ ምርጫቸው ማድረጉን የድርጅቱ የአፍሪካ ፕሬዚዳንት ጄም አጉይለር ተናግረዋል፡፡
አምሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው፥ በአገራችን የሚስተዋሉ የፀጥታ ፣ የኮቪድ -19 እና ሌሎች ችግሮች ጊዜያዊ መሆናቸውን ገልጸው፥ ድርጅቱ በአገራችን ላይ እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
መንግስት በአገሪቱ እያካሄደ ያለውን የለውጥ ሥራ በማጠናከር ለግሉ ዘርፍ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኑን ጠቁመው፥ ለግል ባለሀብቶች የሚገጥማቸውን ችግር ለመቅረፍ በኢንዱስትሪ የተሰማሩ ባለሀብቶች ከመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር የምክክር መድረክ እንደሚዘጋጅ አመላክተዋል፡፡
የድርጅቱ ሥራ ኃላፊዎች መንግስት እያካሄዳቸው ያላቸው የለውጥ ሥራዎች ተስፋ ሰጭ መሆናቸውን እንደሚገነዘቡ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.