Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከስልጤ ዞን አስተዳደር እና ሀይማኖት አባቶች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በስልጤ ዞን ተፈጥሮ የነበረው የፀጥታ ችግር ዳግም እንዳይከሰት የደቡብ ክልል የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከዞኑ ባለድርሻ አካላት በጋራ ችግሩን ለመፍታት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ የክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀላፊዎች የአብሮነት እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
ተቋሙ ሃይማኖታዊ ትስስሩን በማጠናከር በእምነቶች መካከል መደጋገፍ፣ መመካከርና መረዳዳት እንዲሰፍን አጠንክሮ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
የስልጤ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሰብሳቢ ሼይክ መሐመድ ኸሊል በበኩላቸው÷ የፀጥታ ችግሩ ባጋጠመ ወቅት የወደሙ ንብረቶችን ከዞኑ ህዝብና መንግስት ጋር በመተባበር መልሶ የማቋቋም ስራ እየተከናወነ መሆኑን እና በቀጣይም ይህ በተሻለ መልኩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የስልጤ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ አሊ ከድር የዞኑ ህዝብ በሀገር ሰላም ላይ ድርድር የሌለው ህዝብ መሆኑን በማንሳት ሰሞኑን የተፈጠረው ችግርም ህዝቡን እንደማይወክል ጠቁመዋል።
ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ መንግስት ከማህበረሰቡ በጋራ እየሰራ እንደሆነም ነው ያስታወቁት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.