Fana: At a Speed of Life!

አማዞን የኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ ተገቢ ያልሆነ ዋጋ የጨመሩ 1 ሚሊየን  ምርቶችን  አገደ

አዲስ አበባ፣የካቲት 24፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) አማዞን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን  ምክንያት በማድርግ ያልተገባ ዋጋ የጨመሩ እና የተሳሳቱ መረጃዎችን ያሰራጩ 1 ሚሊየን  ምርቶችን ከገጹ ማስወገዱን አስታውቋል።

ተቋሙ ይህንን እርምጃ የወሰድኩት ደንበኞች የኮሮና ቫይረስ ጋር የተዛመዱ የፊት ጭንብልን የመሳሰሉ ምርቶችን፣ የጭነት መላኪያ ወጪዎች ጨምሮ የመደበኛ ዋጋቸውን አምስት እጥፍ ያህል ዋጋ በመጠየቃቸው ነው ብሏል፡፡

ኩባንያው ባወጣው መግለጫ ላይ ሻጮች በምርት ሽያጭ ዝርዝር ላይ ሁልጊዜ  ትክክለኛውን መረጃ እንዲያቀርቡ ፖሊሲው  መጠየቁን አስታውሶ፥ ይህንን ፖሊሲ የሚጥሱትን   ደግሞ ከዝርዝሩ ያስወግዳል ብሏል  ፡፡

አለም የጤና ሁኔታ ስጋት ውስጥ በወደቀበት በዚህ ወሳኝ  ወቅት በዋነኛነት በሚያስፈልጉ ምርቶች ላይ  አላስፈላጊ ዋጋ የሚጨምሩት ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ተሰምቶናል ብለዋል፡፡

ይህ እርምጃ በሌሎች ቦታዎች ላይ ከታዩት ዋጋው ከፍ ያለ  ዋጋ መሸጥና ደንበኞችን ለማሳሳት የሚሞክሩትን ይጨምራል ማለቱም ተሰምቷል፡፡

በዚህም የሦስተኛ ወገን ሻጮች የኩባንያውን ፍትሃዊ የዋጋ ፖሊሲ መከተል እንዳለባቸው አሳስቧል።

ለረጅም ጊዜ ከቆየው ፖሊሲያችን በተጻራሪ በሰሩት  ደንበኞች ላይ ኩባንያው በቅርብ ጊዜ  በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አቅራቢዎችን ማስወገዱን  ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም የተቋሙን መመሪያዎች የሚጥሱ አቅርቦቶችን የመቆጣጠርና የማስወገዱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ቀድም ሲል በአማዞን ላይ ያሉ የሶስተኛ ወገን ሻጮች የተጭበረበሩ ምርቶችን በመሸጥ ትችት ሲሰነዘርባቸው እንደነበር ተመላክቷል፡፡

ምንጭ፡-ሲ.ኤን.ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.