Fana: At a Speed of Life!

ኢራን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር  54 ሺህ እስረኞችን በጊዜያዊነት ፈታች

አዲስ አበባ፣የካቲት 25፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢራን ብዙ ዜጎች በሚገኙባቸው ማረሚያ ቤቶች ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቆጣጠር 54 ሺህ እስረኞችን በጊዜያዊነት መፍታቷ ተሰምቷል።

እስረኞቹ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አድርገው ነጻ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ በዋስ ከእስር መፈታታቸውን የሀገሪቱ ፍርድ ቤት ቃል አቀባይ ጋሆላምሆሴን እስማኤሊ ተናግረዋል።

ውሳኔው ከደህንነት ጉዳይ ጋር በተያያዘ የታሰሩና ከአምስት ዓመት በላይ የተፈረደባቸው እስረኞችን እንደማያካትት ተመላክቷል።

በሌላ በኩል ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ በስለላ ወንጀል ክስ ላለፉት አምስት ዓመታት እስር ላይ የምትገኘው የብሪታኒያ እና የኢራን ዜግነት ያላት የበጎ አድራጎት ሠራተኛ ናዚዋን ዛጊራ-ራትክሊፍ በቅርቡ ልትፈታ እንደምትችል ተጠቁሟል፡፡

በኢራን በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 77 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ 2 ሺህ 336 በላይ የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

በዚህም ኢራን ከቻይና ቀጥላ በቫይረሱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት ሀገር መሆኗ ነው የተገለጸው።

ምንጭ ፦ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.