Fana: At a Speed of Life!

የአራት ክልሎች እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ አመራሮች የምክክር መድረክ ተካሔደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአራት ክልሎች የእንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ አመራሮች ከብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት ጋር የምክክር መድረክ አካሄዱ።

በመድረኩ የኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ እና ደቡብ ክልሎች የተሳተፉ ሲሆን፥ መድረኩ መከላከልን መሠረት ያደረገ የእንስሳት በሽታ መከላከያ ክትባት ስርጭት፣ አሰጣጥ እና ተያያዥ ችግሮች ላይ በመወያየት መፍትሔ ማስቀመጥን መሰረት ያደረገ ነው ተብሏል።

የብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት የእንስሳት ክትባትን የማምረት፣ የማሰራጨት፣ የመስክ ክትትል፣ የምርምር እና ክትባት የማልማት ተሞክሮ ቀርቧል።

የየክልሎቹ የዘርፉ የሥራ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎችም የየክልሎቻቸውን ተሞክሮ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ የሥጋ እና ወተት ሀብት ልማት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኢንስቲቲዩቱ የቦርድ አመራር አባል አቶ ታደሰ ጉታ፥ ለሚነሱ ችግሮች መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።

የብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማርታ ያሚ በበኩላቸው፥ ውይይቱ ተቋሙ ለሚሰራቸው ስራዎች አቅጣጫ የማስቀመጥ ስራ አካል መሆኑን አስረድተዋል።

መረጃው የብሄራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት ነው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.