Fana: At a Speed of Life!

የዓይኖቿን ውበት ለመጨመር ያደረገችው ድርጊት ዕይታዋን ያሳጣት ወጣት

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፖላንዳዊቷ ወጣት የዓይኖቿን ውበት ለመጨመር ያደረገችው ድርጊት የቀኝ ዓይኗን ዕይታ አሳጥቷታል።

ወጣቷ ውበቷን ለመጨመር የሰውነት ላይ ንቅሳት የሚሰሩ ባለሙያዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጾች አፈላልጋ ታገኛለች።

በመቀጠልም ባለሙያው የአይኖቿን ውስጣዊ ክፍል ማሳመር የሚያስችል ንቅሳት እንዲሰራላት ተስማምተው ባለሙያውም ስራውን ይጀምራል።

ይሁን እንጅ በንቅሳት ስራው ሂደት ላይ ባለሙያው በፈጠረው ስህተት ምክንያት አይኖቿ ለከፍተኛ ህመም ይዳረጋሉ።

በአንፃሩ ባለሙያው በስራው ሂደት ላይ የሚያጋጥም የተለመደ የህመም ስሜት መሆኑን በመግለጽ የማስታገሻ መድሃኒት እንድትወስድ ያደርጋል።

ይሁን እንጅ ወጣቷ የአይኖቿን ውበት ለመጨመር ያሰበችው ድርጊት ውጤቱ የከፋ ሆኖ የቀኝ አይኗን እይታ ሙሉ በሙሉ ማሳጣቱ ነው የተነገረው።

ከዚህ ባለፈም የግራ አይኗ የእይታ አድማስ ችግር እንዳጋጠመው ተገልጿል።

ከስተቱን ተከትሎ ወጣቷ የአይኖቿን ብርሃን ለመታደግ የተለያዩ ቀዶ ጥገና ህክምናዎችን ብታደርግም ኦፕቲክ ነርቭ የተባለው የአይኗ ክፍል ስለተጎዳ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

የንቅሳት አርቲስቱም ክስ ተመስርቶበት የሦስት ዓመት እስራት ተወስኖበታል፡፡

ወጣቷ ትክክለኛ ሰው ጋር አለመሄዷ እንጅ ንቅሳት በመሰራቷ እንደማትቆጭ ተናገራለች፡፡

ምንጭ፦ ኦዲቲ ሴንትራል

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.