Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከማላዊ እና ግብፅ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ዝግጅት ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አቀረበ፡፡

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚመሩት ዋልያዎቹ በግንቦት 25 እና 29 ከማላዊ እና ግብጽ ብሄራዊ ቡድኖች ጋር የ2023 አፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ በማላዊ ዋና ከተማ ሊሎንግዌ በሚገኘው ቢንጉ ስቴዲየም ያከናውናሉ፡፡

ለዚህም ዝግጅት እንዲረዳ አሰልጣኝ ዉበቱ አባተ ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡

በዚህም መሰረት∶-

ግብ ጠባቂዎች

ፋሲል ገብረሚካኤል፣ በረከት አማረ፣ ዳግም ተፈራ፣ ሰኢድ ሀብታሙ

ተከላካዮች

አስራት ቱንጆ፣ ረመዳን ዬሱፍ ፣ ሱሌይማን ሀሚድ፣ ብርሃኑ በቀለ፣ ምኞት ደበበ፣ ያሬድ ባዬ፣ ጊት ጋትኩት፣ ሚሊዮን ሰለሞን

አማካዮች

አማኑኤል ዩሃንስ፣ ጋቶች ፓኖም፣ ሱራፌል ዳኛቸው፣ በዘብህ መለዮ፣ መስኡድ መሀመድ፣ ቢኒያም በላይ፣ ወንድማገኝ ሀይሉ፣ ሽመልስ በቀለ

አጥቂዎች

አማኑኤል ገብረሚካኤል፣ ቸርነት ጉግሳ፣ ዳዋ ሆቴሳ፣ በረከት ደስታ፣ አቡበክር ናስር፣ ይገዙ ቦጋለ እና ሀብታሙ ታደሰ ጥሪ እንደተደረገላቸው ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.