Fana: At a Speed of Life!

በአረርቲ ከተማ ለሚገኙ 1 ሺህ 447 ተፈናቃዮች የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአረርቲ ከተማ ለሚገኙ 1 ሺህ 447 ተፈናቃይ ወገኖች የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ተደረገ፡፡

ድጋፉ ከሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማዕከል የተላከ ሲሆን ፥ 220 ኩንታል የምግብ ስንዴ፣ 100 ካርቶን ብስኩት፣ 400 ልባሽ ጨርቅ እና 10 ካርቶን የሴቶች የንጽህና መጠበቂያን ያካተተ ነው፡፡

በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ቦሰትና የወረዳው አደጋ መከላከልና ዝግጁነት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የሚንጃር ሸንኮራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተመሳሳይ በደቡብ አፍሪካ ኡምታታ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባባ የአማራ ወጣቶች ማህበር ጋር በመተባበር ግምቱ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሆነ የአይነት ድጋፍ በዋግ ኽምራ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ድጋፉም÷ የስንዴ ዱቄት ፣ አልባሳት ፣ የትምህርት ቁሳቁስና የንፅህና መጠበቂያ ሲሆን÷ በሰቆጣ ወለህ መጠለያ ጣብያ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች መሰጠቱን ከዋግ ኽምራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.