Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል መሰናክሎችን በመቋቋም ግዳጁን በስኬት እየፈፀመ ይገኛል – ሜጀር ጄኔራል ጆይሳኩር ሜኖን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰላም አሰከባሪ ኃይል አስቸጋሪ የመሬት አቀማመጥና መሰናክሎችን በመቋቋም ግዳጁን በስኬት እየፈፀመ እንደሚገኝ በተባበሩት መንግስታት የሠላም ማሰከበር ስትራቲጂክ ግንኝነት ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ጆይሳኩር ሜኖን ተናገሩ።
ጀኔራል መኮንኑ በተባበሩት መንግስታት የስትራቴጂክ ግንኙነት ቡድን ልዑክን በመምራት በደቡብ ሱዳን ምዕራብ አኳቶሪያ የሚገኘውን የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አሰከባሪ ሻለቃ የግዳጅ ቀጠናን ተዘዋወረው ጎብኝተዋል።
የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አሰከባሪ ሻለቃ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ከፍያለው ረጋሳ እና የሻለቃው ከፍተኛ መኮንኖች ለልዑኩ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ፥ ዋና አዛዡ የሻለቃውን የግዳጅ አፈፃፀምም በተመለከተ ገለፃ አድርገዋል።
ሜጀር ጀኔራል ጀይሳኩር ሜኖን ከጉብኝቱ በኋላ ባደረጉት ንግግር ፥ የኢትዮጵያ 15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አሰከባሪ ሻለቃ አባላት በአሰቸጋሪ ሁኔታና ወቅት በቀጣናው የተሰጣቸውን ዓለም አቀፍ ተልዕኮ በብቃት መወጣታቸውን አድንቀዋል።
የሻለቃው አባላት በተመደቡበት የግዳጅ ቀጠና አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ እያከናወኑት ያለው ተግባር የሚደነቅ ስለመሆኑ ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በአካባቢው የመሠረተ ልማት አገልግሎት ባልተሟላበት ሁኔታ ሠራዊቱ ግዳጁን በፅናትና በቁርጠኝነት እየተወጣ አንደሚገኝ በተግባር ማረጋገጣቸውን የገለጹት ሜጄር ጄኔራል ጆይሳኩር ፥ ለተልዕኮ አፈፃፀም ሂደቱ አስፈላጊ የሆኑና በሻለቃው ተልዕኮ ላይ ክፍተት ሊፈጥሩ የሚችሉ ችግሮችን በፍጥነት እንዲሟሉ እናደርጋለን ብለዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.