Fana: At a Speed of Life!

በዳይመንድ ሊግ የ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2022 ዳይመንድ ሊግ በእንግሊዝ በርሚንግሃም ከተማ ተካሂዷል።

በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

በዚህም ዳዊት ስዮም 14:47:15 በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ ሌላዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት ሃዊ ፈይሳ 14:48.94 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

እንዲሁም ፋንቱ ወርቁ 14:49.68 በመግባት ውድድሩን በሶስተኝነት ማጠናቀቋን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.