Fana: At a Speed of Life!

ሩስያ 963 አሜሪካውያንን እና 26 ካናዳውያንን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩስያ 963 አሜሪካውያን እና 26 ካናዳውያን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ማገዷን አስታወቀች፡፡

የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው፥ 963 አሜሪካውያን መቼም ቢሆን ወደ አገሯ እንዳይገቡ ያገደች ሲሆን፥ እገዳው ከተጣለባቸው አሜሪካውያን መካከል በዋናነት ጆ ባይደን እና ልጃቸው ሀንተር ባይደን ይገኙበታል፡፡

የአሜሪካ ባለሥልጣናት ÷ የአሜሪካ ህዝብ በሩስያ ላይ የተዛባ አመለካከት እንዲይዝና ጥላቻ እንዲያድርበት እየሠሩ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ መግለጡንና ድርጊቱን መኮነኑን ታስ የተሰኘው የሀገሪቷ የዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

በተመሳሳይ ወደ ሩሲያ እንዳይገቡበ ያታገዱት 26ቱ ካናዳውያን ፣ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ በመስጠታቸው ነው ተብሏል፡፡

ከታገዱት ካናዳውያን መካከልም በዋናነት የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ እና ባለቤታቸው እንደሚገኙበት ነው ሽንዋ የዘገበው፡፡

ሩሲያ የአሜሪካ ባለስልጣናትንና ህዝብን ለይታ እንደምትመለከት፥ እንዲሁም ከየትኛውም ሀገር ጋር ግጭት እንደማትፈልግ እና በሯ ምንጊዜም ለውይይት ክፍት መሆኑን የሀገሪቷ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.