Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለሐረሪ ክልል ባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ ተዘጋጅቷል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለሐረሪ ክልል ባህል ማዕከል መገንቢያ ቦታ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

“የሸዋል ኢድ” በአዲስ አበባ ሃይማኖታዊና ባሕላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የተከበረ ሲሆን ፥ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ለሐረሪ ባህል ማእከል መገንቢያ ቦታ መዘጋጀቱንም አብስረዋል፡፡

ከንቲባዋ አክለውም ፥አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ነች፤ ይህን ውብ የሸዋል ባህል ከሌሎች ባህሎቻችን ጋር አዋህደን የአብሮነት መድመቂያ እንዲሆን ከተማ አስተዳድሩ ይደግፋል፤ አብሮም ይሰራል ብለዋል፡፡

እኛ ኢትጵያውያን የብዙ ደማቅና ውብ ባህሎችና ወጎች ባለቤት ብንሆንም፥ የሌሎችን ባህልና ማንነት በፍቅር ይዘን ስንከባከብ አንድነታችን የበለጠ ይጎለብታል ማለታቸውን ከመዲናዋ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.