Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት የማደስ መርሐ ግብር አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በአርባምንጭ ከተማ የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት የማደስ መርሐ ግብር አስጀመሩ።

የፓርቲው አመራሮች “አዲስ ፖለቲካዊ እይታ፥ አዲስ ሀገራዊ እምርታ” በሚል መርህ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና በአርባምንጭ ከተማ እየወሰዱ ይገኛሉ።

በጋሞ ዞን የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን የጎበኙት አመራሮች የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አካል የሆነውን ቤት የማደስ መርሐ ግብርን በአርባምንጭ ከተማ አስጀምረዋል።

በአርባምንጭ ከተማ የሚገኙ የአቅመ ደካማ እናት መኖሪያ ቤት የማደስ መርሐ ግብርን በጋራ ያስጀመሩት አመራሮቹ ለማደሻ የሚሆን ገንዘብ በጋራ አስረክበዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና ርዕዮት ዓለም ግንባታ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል ፥ በስልጠናው ላይ ያገኘነውን ሀሳብ በተግባር ትምህርትና የልምድ ልውውጥ ያዳበርንበት ዕለት ነው ብለዋል።

በብልጽግና እሳቤዎች ውስጥ አንዱ ማህበራዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው ያሉት አቶ ስንታየሁ ፥ መደጋገፍ ፣ ማዕድ መጋራትና ደካሞችን መርዳት አንዱ መርህ በመሆኑ በንድፈ ሀሳብ ያገኘነውን በተግባር እያሳዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይህ ተግባር በየአካባቢውና በየመንደሩ እየሰፋ መሄድ አለበት ያሉት አቶ ስንታየሁ ፥ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ያስጀመሩትን የዕድሳት መርሐ ግብር የሁለተኛው ዙር ሰልጣኞች ያጠናቅቁታል ማለታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.