Fana: At a Speed of Life!

በአዳማ ከተማ ከህዝብ አገልግሎት ጋር የተቆራኙ ተቋማትን ወደ ዲጂታል የማስገባት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “በክልሉ ከተሞች ዘርፈ ብዙ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ብልሹ አሰራርና ሌብነትን ለማስወገድ የአገልግሎት አሰጣጥን ወደ ዲጂታላይዜሽን መቀየር አለብን አሉ አቶ አዲሱ አረጋ።

በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ የተመራ የክልሉና የፌዴራል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ የአዳማ ከተማን የዲጂታላይዜሽን ስራ ጉብኝት አካሂዷል፡፡

ህዝቡ ከመንግስት የሚጠብቀው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ነው ያሉት አቶ አዲሱ፥ ይህንን እውን ማድረግና የህዝቡን ጥያቄ መመለስ የምንችለው አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ መደገፍ ስንችል ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

በአዳማ ከተማ በተለይ በመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም፣በመዘጋጃ ቤት አገልግሎት፣ገቢዎችና የንግድ ተቋማትን ወደ ዲጂታላይዜሽን በማስገባት ረገድ ያሉ ጅምር ጥረቶች የሚበረታቱና ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃይሉ ጀልዴ በበኩላቸው÷ የከተማዋን አገልግሎት ወደ ዲጂታላይዜሽን ለመቀየር ያስፈለገው የህዝቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመመለስ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዚህም የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ዘመናዊ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ካዳስተር ስርዓት፣የገቢና የንግድ ተቋማት ማዘመንና ከህዝብ አገልግሎት ጋር የተቆራኙ ተቋማትን ወደ ዲጂታል የማስገባት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

ወንጀልና ህገ ወጥ አሰራርን ለመከላከል የአዳማ ከተማን መሰረት ያደረገ አዳማ ፖርታል የመረጃ መቀበያ ሲስተም መዘርጋቱንም ከንቲባው ገልጸው፥ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ በቴክኖሎጂ ተደግፎ እየተሰጠ እንደ እንደ ኢዜአ ዘገባ መሆኑንና ዘመናዊ የቤቶች አስተዳደር ስርዓት፣የገቢ አሰባሰብና ማሻሻያ ላይ አዲስ ሶፍትዌር በማበልፀግ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.