Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎችን በጋምቤላ ከተማ በይፋ አስጀምረዋል።
 
የክልሉ ርዕሰ መተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የበጎ ፍቃድ የአገልግሎቱን ሲያስጀመሩ እንዳሉት፥ አመራሩ ከመደበኛ የልማት ስራዎች ጎን ለጎን የክረምት በጎ ፍቀድ አገልግሎት ስራዎች ህዝቡን በማስተባበር በትኩርት እንዲሰሩ አሳስበዋል።
 
በተለይም በክረምቱ ወራት በአቅመ ደካማ ቤቶች ጥገና፣ በተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ፣ በአካካቢ ጽዳትና በሌሎች ዘርፎች አመራሩ በትጋት ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።
 
የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተንኩዌይ ጆክ በበኩላቸው ፥ የክረምቱን ወራት ተከትሎ የሚከሰቱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የአካባቢን ንፅህና መጠበቅ ይገባል ብለዋል።
 
በመሆኑም በክልል ደረጃ በአመራሩ የተጀመረዉ አካባቢን የማፅዳትና የአቅመ ደካቤ ወገኖችን ቤት የማደስ ተግባር በሁሉም የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።
 
በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ላክደር ላክባክ በበኩላቸው ፥ የብልጽግና ፓርቲ ሰሞኑን ለከፍተኛ አመራሩ በሰጠው ስልጠና የተዛቡና አግላይ እሳቤዎችን በአዲስ ፖለቲካዊ እይታ እንዲተካ አድርጓል ማለታቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.