Fana: At a Speed of Life!

ለምርመራ ወደ ውጪ የሚላኩ ናሙናዎችን የሚያስቀር የላቦራቶሪ ማሽን በጅማ ዩኒቨርሲቲ ተተከለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለምርመራ ወደውጪ የሚላኩ ናሙናዎችን የሚያስቀር የላቦራቶሪ ማሽን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የጤና ማዕከል ተተከለ፡፡

በሪቲና ፋርማቲካል አማካይነት የተተከለው ኮባስ 6800 ማሽን በሰዓት 834 ናሙናዎችን የሚቀበል ሲሆን ፥ ወደ ውጪ አገር የሚላኩ ምርመራዎችንም በማስቀረት ህብረተሰቡን ከከፍተኛ ወጪ እንደሚታደግ ታምኖበታል።

5 ሚሊየን ገደማ ያወጣል የተባለው የላብራቶሪ ማሽን ለየት የሚያደርገው የኤች አይ ቪን እና የጉበት ቫይረስን ጨምሮ ሌሎች ቫይረሶችን ለመለየት የሚያስችል ከመሆኑም በላይ ለማህጸን ካንሰር ምርመራ ይውላል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ተወካይ አቶ ፈይሳ ጫላ ማሽኑ ለሆስፒታሉ በነፃ የተሰጠ ሲሆን÷ ይህም በኢትዮጵያ ሶስተኛው ማዕከል መሆኑን አስረድተዋል።

የሪቲና ፋርማቲካል ተወካይ አቶ አሸብር ጉርሜሳ በበኩላቸው፥ ባለሞያዎችን በማሰልጠን የተቀላጠፈና ጥራት ያለዉ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እንዲደርስ ኩባንያው የተቻለውን ያደርጋል ብለዋል።

በአቤኔዘር ታዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.