Fana: At a Speed of Life!

ምዕራብ ዕዝ የጠላትን ኃይል ድባቅ መምታት የሚችል የሜካናይዝድ ኃይል መገንባቱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምዕራብ ዕዝ የጠላትን ኃይል ድባቅ መምታት የሚችል የሜካናይዝድ ኃይል መገንባቱን ገለፀ።
በምዕራብ ዕዝ የሜካናይዝድ ክፍል አስተባባሪ ኮሎኔል ታደሰ ተበጀ እንደገለፁት÷ የተኩስ አመራሩ እና የምድብተኛ ኃይሉ ያለፈውን የጦርነት ጊዜያት መነሻ ያደረገ በቂ ዝግጅት አድርጓል፡፡
በሁሉም የሜካናይዝድ ኃይል ወታደራዊ ስልጠናዎች ተካሂደዋል ያሉት ኮሎኔል ታደሰ÷ የሜካናይዝድ ክፍሎች የሚሰጣቸውን ግዳጅ ተቀብለው የጠላትን ኃይል ድባቅ ለመምታት የላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
ሰራዊቱ ካካሄዳቸው ውጊያዎች በርካታ ልምዶችን በመውሰድ በሁኔታዎች መሃል በየጊዜው የሜካናይዝድ ኃይሉን የማድረግ አቅም ማሳደግ መቻሉንም ነው የገለጹት፡፡
የሜካናይዝድ ክፍሎች ለእግረኛ ክፍለ ጦሮች የተኩስ ድጋፍ ለመስጠት እና የጠላትን ኢላማዎች በአስተማማኝ ሁኔታ ለማውደም ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁች ናቸው ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.