Fana: At a Speed of Life!

አመራሩ አሁን እየገጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በጽናት በመታገል ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ በትጋት እንዲሰራ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ሃላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ አመራሩ አሁን እየገጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በጽናት በመታገል ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ በትጋት እንዲሰራ ጠየቁ።

በሐረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች “አዲስ ፖለቲካዊ እይታ – አዲስ አገራዊ እመርታ ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሰጥ የነበረው የመጀመሪያ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና መጠናቀቁ ተገልጿል።

በስልጠና ማጠቃለያው ላይ የተገኙት አቶ አብዱጀባር መሀመድ ÷ ኢትዮጵያን ከፈተናዎቿ ሊያሻግራት የሚችል ብቁ አመራር መፍጠር የብልጽግና ፓርቲ አንዱ አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጀመሪያው የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ የተቀመጡ የሥራ አቅጣጫዎችን በዕቅድ በመያዝ ወደ ተግባር መገባቱንም ገልጸዋል።

በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ከህብረተሰቡ ለሚነሱ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በተጠናከረ መልኩ ሊሰሩ እንደሚገባም አመላክተዋል።

አመራሩ አቅሙን በማጎልበት ወቅቱን የሚመጥን አመራር መስጠት እንደሚጠበቅበት ጠቅሰው÷የክልሉን ህዝብ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ለማድረግ አመራሩ በቁርጠኝነት ሊሰራ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ተመሳሳይ የስልጠና መድረኮች እስከታችኛው የአመራር እርከን ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.