Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዘረኝነትን ማስወገድ በሚቻልበት አግባብ ላይ ለመምከር ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ዘረኝነትን ማቆም የሚቻለው የሰውን አመለካከት በመቀየር ብቻ ሳይሆን በጥቁር እና በነጭ መካከል ያለውን የኑሮ ልዩነት ማጥበብ ሲቻል ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ይህን ያሉት በደቡብ አፍሪካ ስቴለን ቦሽ ዩኒቨርሲቲ አንድ ነጭ ተማሪ በጥቁር የዩኒቨርሲቲው ተማሪ ደብተር ላይ በመሽናት ክብር የሚነካ ድርጊት ከፈጸመ በኋላ አመፅ መቀስቀሱን ተከትሎ ነው።

በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫም ደቡብ አፍሪካውያን ዘረኝነትን ለማስወገድ ሃቀኝነት እና ግልጽነት የታከለበት ውይይት ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።

ራማፎሳ በመልዕክታቸው ተማሪዎች መቻቻልንና ብዝሃነትን እንዲያከብሩ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ የማስረፅ ሥራ ሊሰራ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል።

እንደ ራማፎሳ ÷ተማሪዎች እንደ ዘረኝነት፣ አድልዖ ፣ ማግለልና ፆታዊ ጥቃት ያሉ ክብረ-ነክ ድርጊቶች የሚያንጸባርቁት ከቤተሰቦቻቸው አይተው በመሆኑ የባህሪ ቀረጻው እነሱንም ማካተት እንዳለበት አመላክተዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ተማሪዎች ኅብረት የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ተማሪ ድርጊቱን በተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ማጋራቱን ጠቅሶ፥ ሁኔታው ቁጣውን እንዳባባሰው እና ቀስ በቀስ ወደ ተማሪዎች አመፅ እንዳደገ አስረድቷል፡፡

ኅብረቱ እንደዚህ አይነት የዘረኝነት ድርጊቶችን አጥብቆ እንደሚቃወም መግለጹን የሲ ጂ ቲ ኤን እና ኒውስ 24 ዘገባ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.