Fana: At a Speed of Life!

የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለመሰማራት ያላቸውን ፍላጎት ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህንድ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በማዕድን፣ በአምራች ዘርፍ፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በአይ ሲ ቲ እንዲሁም በትምህርት ዘርፎች ለመሰማራት ያቸውን ፍላጎት ገለጹ፡፡
ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ እና ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ ከህንድ የመጡ ባለሀብቶች እንዲሁም ከህንድ ኢኮኖሚና ንግድ ተቋም ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ የኢትዮጵያ መንግስት ኢንቨስትመንት የመሳብ ዕቅድን ማዕከል በማድረግ ግብዣ የተደረገለት ሲሆን፥ በኢትዮጵያ በማዕድን፣ በአምራች ዘርፍ፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በአይ ሲ ቲ እንዲሁም በትምህርት ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎትን አሳይቷል፡፡
ከውይይቱ በኋላ ባለሃብቶቹ የቡልቡላ፣ የቦሌ ለሚ እና የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን መጎብኘታቸውን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.