Fana: At a Speed of Life!

በቴክሳስ የ18 ዓመት ተጠርጣሪ በተኩስ እሩምታ 19 ህጻናት እና 2 ጎልማሶችን ገደለ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ደቡብ ቴክሳስ በሚገኝ አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በደረሰ ጥቃት 19 ህጻናት እና ሁለት ጎልማሶች ተገደሉ፡፡

የ18 ዓመት ተጠርጣሪ ወጣት ከሰባት እስከ 10 ዓመት ዕድሜ ያላቸውን ሕፃናት በሚያስተምር ሮብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በከፈተው የተኩስ እሩምታ ነው የ19 ህጻናት ተማሪዎችን እና የ2 ጎልማሶች ህይወትን የቀጠፈው።

ተጠርጣው ወጣት በአከባቢው የሚገኝ የአንድ የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሳይሆን እንዳለቀረ የተገለጸ ሲሆን፥ ከዚህ ቀደም በሴት አያቱ ግድያም እንደሚጠረጠር ዘገባዎች ጠቁመዋል።

ጥቃት አድራሹ በሕግ አስከባሪዎች እንደተገደለ የተገለጸ ሲሆን፥ ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት ሽጉጥ እና ኤ አር-15 ከፊል አውቶማቲክ ጠመንጃ ይዞ እንደነበር መርማሪዎች መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.