Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከኮካ ኮላ ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኮካ ኮላ ኩባንያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኮካ ኮላ ሊቀ መንበር ጄምስ ኩይንሲ እና የኮካ ኮላ ኩባንያ የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጃኩዬስ ቨርሚዩለን ጋር ነው የተወያዩት።

በውይይታቸው ወቅትም ኮካ ኮላ በመጭው ክረምት በሃገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል ለታቀደው የ5 ቢሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጧል።

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለማድረግ ቃል መግባቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ኮካ ኮላ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትን ለማስፋፋትና በአዲስ አበባ እየተተገበሩ ላሉ ፕሮጀክቶች የሚያደርገውን ድጋፍ አድንቀዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.