Fana: At a Speed of Life!

የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ምርቶችን በዱቤ መግዛት የሚያስችል አሠራር ለመዘርጋት ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ተደራሽ ባልሆነባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ምርቶችን በዱቤ በመግዛት መጠቀም የሚችሉበትን አሠራር ለማበጀት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ፡፡

በውይይቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ የዓለም ባንክ አማካሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሱልጣን ወሊ የመድረኩ ዓላማ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅቶችን ከተጠቃሚዎች ጋር ማገናኘት መሆኑን ገልጸው÷ በዚህም ከብሔራዊ የኤሌክትሪክ ግሪድ ርቀው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተጠቃሚዎች “ፔይ አስ ዩ ጎ” በተሰኘ ቢዝነስ ሞዴል ቅድሚያ አነስተኛ ክፍያ በመፈፀም የሶላር ቴክኖሎጂ ምርቱን ተጠቃሚ እንደሚሆኑና ቀሪ ክፍያቸውንም ከስልኮቻቸው ጋር በማያያዝ የሚከፍሉበት እንዲሁም ክፍያቸውን ሲጨርሱም የምርቱ ባለቤት እንዲሆኑ የሚያስችል አሠራር መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.