Fana: At a Speed of Life!

ቻይና በሀገር በቀል የልማት መርህዎቿ የማንንም ጣልቃ ገብነት እንደማትሻ አስገነዘበች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ራስን በራስ የማስተዳደር እና የመልማት መብት ቀዳሚ የሰብዓዊ መብቶች መሆናቸውን አስገነዘበች፡፡

የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ለተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ሀላፊ ሚሼል ባችሌት እንደተናገሩት ÷ በሀገራት ጉዳዮች ላይ የውጭ ኃይላት ጣልቃ ገብነት አፍራሽ ሚና አለው፡፡

ሺ ጂንፒንግ ከሚሼል ባችሌት ጋር በበይነ-መረብ ሲወያዩ ፥ በእኩልነት ላይ የተመሠረተ መከባበር ስለ ሰብዓዊ መብት ለመነጋገር መሠረት ነው ብለዋል፡፡

ሺ፥ የሰብዓዊ መብቶችን መከበር ለማረጋገጥና ጥራቱን የጠበቀ፣ ውጤታማነት የታከለበት፣ ሊተገበር የሚችል እና ዘላቂ ደኅንነትን የሚያረጋግጥ ጥበቃ በሀገራቸው ዕውን ለማድረግ አሁንም በርካታ ሥራዎች መተግበር እንዳለባቸው አልሸሸጉም፡፡

ሺ፥ ቻይና ከታሪኳ እና ከባሕሏ የቀዳችው የህዝቦቿን ሰብዓዊ መብቶች መከበር የምታረጋግጥበት መንገድ እንዳለ ገልጸው፥ ሀገራት ሰብዓዊ መብቶችን በራሳቸው አውድ የሚተገብሩበት መንገድ ሊከበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ብያኔ ከሀገራት ታሪክ፣ ባሕል፣ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ፣ ማኅበራዊ ሥርዓት እና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አንጻር የሚታዩ መሆናቸውንም አስምረውበታል፡፡

መሬት ላይ ያለውን ዕውነታ ሳይመለከቱ ሥርዓትን ወይም ሞዴልን ከሌላ ሀገራት በጭፍን ቀድቶ ለመተግበር መሞከር ሀገር ማፍረስ መሆኑንም መናገራቸውን አናዱሉ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.