Fana: At a Speed of Life!

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የግሉን ዘርፍ በቀዳሚነት እንዲሳተፍ ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂው ዘርፍ ለኢኮኖሚያዊ እድገት የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ የግሉን ዘርፍ በቀዳሚነት እንዲሳተፍ ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ከግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በዘርፉ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት እያደረገ ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሁሪያ አሊ፥ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚያዊ እድገት የሚኖረው ሚና ቀላል የሚባል ባለመሆኑ የግሉ ዘርፍ በቀዳሚነት እንዲሳተፍ ማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

ዘርፉ ለስራ እድል ፈጠራም ያለው ጠቀሜታ ጉልህ በመሆኑ የፖሊሲ ማሻሻያው የሚፈጥረውን ለውጥ ተግባራዊ በማድረግ የሰዎችን ህይወት ለመቀየር መስራት ይገባልም ነው ያሉት።

ለተጨማሪ መረጃ ቪዲዮውን ይመልከቱ፡-

 

https://www.youtube.com/watch?v=B-Fv6Y45q5w

 

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፉን ለማጠናከር ከ2004 ዓ.ም በኋላ በዚህ ዓመት የፖሊሲ ማሻሻያ መደረጉም በውይይቱ ተገልጿል።

በዘመን በየነ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.