Fana: At a Speed of Life!

10ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ባዛርና አውደ ርዕይ ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ባዛርና አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል በዛሬው ዕለት ተከፍቷል።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጅነር እንዳወቅ አብጤ እና የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጋቱ ዳኛቸውን ጨምሮ የተለያዩ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ባዛርና አውደ ርዕዩ “ቴክኒክና ሙያ የወጣቱ የስኬት በር በሚል መሪ ቃል” ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።

በባዛሩ ላይ ከ500 በላይ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ እንዲሁም የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እንደሚቀርቡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ተናግረዋል።

ኢንጀነር እንዳወቅ አብጤ በበኩላቸው ተቋማት የግብርና ዘርፉን ወደ ኢንዱስትሪ ለማሸጋገር በሚያደርጉት ጥረት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ የማሰልጠኛ ተቋማቱን አቅም ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

በሹመት አለማየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.