Fana: At a Speed of Life!

ሀገርን ማፅናት የሚቻለው በበጎ አመለካከት በመሆኑ ዜጎች በጎ ፈቃደኝነትን ባህል ማድረግ አለባቸው- አቶ ታዬ ደንደአ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገርን ማፅናት የሚቻለው በበጎ አመለካከት በመሆኑ ዜጎች በጎ ፈቃደኝነትን ባህል ሊያደርጉ እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደአ ተናገሩ፡፡
አቶ ታዬ ደንደአ በብሄራዊ ወጣቶች በጎ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው የዜጎችን ሰላም ለመጠበቅ እና ለማረጋገጥ ከፌደራል እና ከክልል መንግሥታት ጋር በመተባበር በህብረሰተቡ ውስጥ ሰላም እና የመተባበር እንዲሁም የመከባበር እና የመቻቻል ባህል እንዲዳብር ተደርጓል ብለዋል፡፡
“በጎነት ለአብሮነት” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የወጣቶች በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት÷ ኢትዮጵያዊ እሴቶችን እና መርሆዎችን ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ውጤቶች ታይተውበታል ያሉት አቶ ታዬ÷ ሀገርን ማፅናት የሚቻለው በበጎ አመለካከት በመሆኑ ዜጎች በጎ ፈቃደኝነትን ባህል ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ የተመረቁ ከ116 ሺህ በላይ ወጣቶች ከመላ ሀገሪቱ መመዝገባቸውን ጠቁመው÷ እስካሁን ከ25 ሺህ በላይ ወጣቶች የ45 ቀናት ስልጠና መውሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም ለስምንት ሺህ ወጣቶች ስልጠና ለመስጠት መታቀዱን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
ስልጠና የወሰዱት በጎ ፈቃደኞች ከመጡበት አካባቢዎች ውጭ ለአሥር ወራት አገልግሎት እንዲሰጡ ስምሪት መሰጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡
በምንይችል አዘዘው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.