Fana: At a Speed of Life!

በኔዘርላንድስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 19፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኔዘርላንድስ ሔግ ከተማና በአካባቢው ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ጋር በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ፥ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በተደረጉ አገራዊ ጥሪዎች፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመርዳት እና በኢድ እስከ ኢድ ፕሮግራሞች ዳያስፖራው የነቃ ተሳትፎ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ያለው እውነታ እንዲታወቅ ድምጻቸውን ከፍ በማድረግ ለሚኖሩብት ሀገር እና መንግስት ሲሞግቱ የነበሩ የዳያስፓራውን አባላትን አመስግነው ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የዳያስፖራ አባላቱ በበኩላቸው ሚሲዮኑ መድረኩን በማዘጋጀቱ አመስግነው፣ ለአገራቸው የሚያደርጉትን ድጋፍ ለማስቀጠል በወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ ላይ የመረጃ ስርጭት በተጠናከረ መልኩ እንዲዳረስ፣ ማህበረሰቡን የሚከፋፍሉ አካሄዶችን ተከታትሎ ወቅታዊ እርምጃ እንዲወሰድ አሳስበዋል፡፡

ከዳያስፖራው በተነሱት ጉዳዮች ላይ አምባሳደር ሒሩት ዘመነ እንዲሁም በሚሲዮኑ ምክትል መሪ አምባሳደር ሻሜቦ ፊታሞ እና የዳያስፖራ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ በርይሁን ደጉ ዝርዝር ማብራሪያና ምላሽ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.