Fana: At a Speed of Life!

አየር ኃይል ኢትዮጵያን በንቃት ለመጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ የዝግጅት ደረጃ ላይ ይገኛል – ሌ/ጀኔራል ይልማ መርዳሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አየር ኃይል ኢትዮጵያን በንቃት ለመጠበቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ በላቀ የዝግጅት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ ገለጹ፡፡
አየር ኃይል በኤር ፖሊስ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት ዛሬ አስመርቋል፡፡
የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የጀግኖች መፍለቂያ ወደ ሆነውና ሁሌም ጀግንነት ከማይለየው አየር ኃይል በመቀላቀላችሁ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል።
አየር ኃይል በአሁኑ ወቅት የሪፎርም ስራዎችን በማከናወን በዘመናዊ ትጥቆችና በተማረ የሰው ኃይል እራሱን በማደራጀት እና በማዘመን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን ከማንኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቶች ለመጠበቅ አየር ኃይል በላቀ የዝግጅት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጣቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
የአየር ኃይል ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ሻለቃ ወንዱ ወልዱ እንደገለጹት÷ ተመራቂዎቹ ከተለያዩ ማሰልጠኛ ማዕከላት የተሰጣቸውን የመሰረታዊ ውትድርና ስልጠና በአጥጋቢ ውጤት ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.