Fana: At a Speed of Life!

ሀገር አቀፍ የመቀንጨር መጠንን ከ60 በመቶ  ወደ 37 በመቶ መቀነስ ተችሏል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)  ሀገር አቀፍ የመቀንጨር መጠንን ከ60 በመቶ  ወደ 37 በመቶ መቀነስ መቻሉ ተገለጸ።

የጤና ሚኒስቴር የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶችንና የአጋር ድርጅቶችን የስድስት ወራት አፈፃፀም በተመለከተ የምክክር መድረክ አከሂዷል።

በዚህ ወቅትም  በስርዓተ ምግብ ዙሪያ በተሰሩ ስራዎች ሀገር አቀፍ የመቀንጨር መጠንን ከ60በመቶ  ወደ 37በመቶ  የቀነሰ  መቻሉን በሚኒስቴሩ የእናቶችና ህፃናት ዳይሬክተር ዶክተር መሰረት ዘላለም ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በመድረኩ የተሻለ አፈፃጸም ላሳዩ ከአማራ ክልል ለደሃና፣ ዝቋላና ጋዞእንዲሁም ከትግራይ ክልል አፍላና ቆላ ተንቤን ወረዳዎች ዕውቅና የተሰጠ መሆኑን  ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.