Fana: At a Speed of Life!

መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ተቋም በአሸባሪ ቡድኑ ለተፈናቀሉ ወገኖች የ 7 ሚሊየን በር የአይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ”ሃና ፋውዴሽን” የተሰኘ መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው ምግባረ-ሠናይ ድርጅት በአሸባሪው ህወሓት ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ጃራ መጠለያ ለሚገኙ ወገኖች ሰባት ሚሊየን ብር የሚያወጣ የዓይነት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን በአዲስአበባ በውክልና የተረከበው የ”ትረስት ፈንድ” ግብረ-ሠናይ ድርጅት በአቶ ዮናስ ሸዋዬ በኩል “ድጋፉ በአሸባሪ ቡድኑ ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ጃራ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች እንዲደርስ ሰጥተዋል፡፡

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ከሚገኘው ”ሃና ፋውዴሽን” የተላከው ድጋፍ በመጠለያው ለሚገኙ ከሕፃናት እስከ አዋቂ የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚደርስ የጫማዎችና የአልባሳት ድጋፍ እንደሆነ ተገልጿል።

35 ሺህ 835 የሚሆኑት የተለያዩ አልባሳት ግምታዊ ዋጋቸው ሰባት ሚሊየን ብር እንደሆነ ተወካዩ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.