Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በፖሊሳዊ ኢንተለጀንስ ሙያ ያሠለጠናቸውን የፖሊስ አመራሮችና አባላት አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በፖሊሳዊ ኢንተለጀንስ ሙያ ያሠለጠናቸውን የፖሊስ አመራሮችና አባላት በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡
ተቋሙ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ባለሙያዎች አማካኝነት ያሠለጠናቸው የፖሊስ አመራሮችና አባላት በወንጀል መከላከልና በምርመራ ሥራ ላይ መረጃ መር የሆነ ፖሊሳዊ ሥምሪት መሥጠት እንዲችሉ ሆነው መሠልጠናቸው ተመልክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ፥ “ተመራቂዎች የሥራ ስምሪት በመውሰድ ክፍተቶችን እንደምትሞሉና የህዝብ ደኅንነት እንደምታረጋግጡ ብሎም ለማናቸውም ተልዕኮ ብቁ በመሆን በጥብቅ ፖሊሳዊ ስነ ምግባር እንደምትሰሩ አምናለሁ” ብለዋል፡፡
በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከፍተኛ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል የፖሊስ ኮሚሽነሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.